Skip to content

Latest commit

 

History

History
410 lines (209 loc) · 51.1 KB

amharic.md

File metadata and controls

410 lines (209 loc) · 51.1 KB

BBC News አማርኛ

ማራቶንን በክብረ ወሰን በማሸነፍ ታሪክ እያስመዘገበች ያለችው ትዕግሥት አሰፋ

ሰኞ 28 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:53:16

ከዓመት በፊት የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ሁለት ደቂቃ በሚጠጋ ጊዜ በማሻሻል ታሪክ ያስመዘገበችው ትዕግሥት አሰፋ፣ እሁድ ለንደን ላይ በተካሄደው የማራቶን ውድድር አሸናፊ ከመሆኗ በተጨማሪ ክብረ ወሰን ለማሻሻል ችላለች። ትዕግሥት በፓሪስ ኦሊምፒክ በሲፋን ሐሰን ተቀድማ ሁለተኛ ከወጣች በኋላ ይህ ውድድር ከባድ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ትዕግሥት የበላይ በመሆን አሸናፊ ሆናለች።

በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰት እብጠት ሁሉ ኪንታሮት ነው? ኪንታሮት ካልታከመ ምን ያስከትላል?

ሰኞ 28 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:53:45

የፊንጢጣ ኪንታሮት ሰዎች ብዙም የማይነጋገሩበት ህመም ነው። አንዳንዶች ሐኪም ለማማከርም ሲያመነቱ ይስተዋላል። ለመሆኑ በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰት እብጠት እና ህመም ሁሉ ኪንታሮት ነው? ሕክምና የሚያስፈልገውስ መቼ ነው? ካልታከመስ ምን ያስከትላል?

አሜሪካ አፍሪካውያን ስደተኞች በሚገኙበት ማዕከል ላይ በፈጸመችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸውን የየመን ሁቲዎች አሳወቁ

ሰኞ 28 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 8:06:50

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ አገራት በርካታ ስደተኞች አደገኛውን የቀይ ባሕር መስመርን በሕገወጥ መንገድ በማቋረጥ ወደ የመን እንደሚገቡ ይታወቃል።

አሜሪካ በየመን ባካሄደችው የአየር ጥቃት ከ800 በላይ ዒላማዎችን መምታቷን አስታወቀች

ሰኞ 28 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 7:01:15

በየመን እየተካሄደ ያለው ውጊያ ከ150 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነ ሲሆን በአገሪቱ ከባድ ሰብዓዊ አደጋን አስከትሏል።

በፍልስጤም የተንቀሳቃሽ ትምህርት ቤት ዲዛይን ውድድር 'ያሸነፉት' ኢትዮጵያውያን አርክቴክቶች

ቅዳሜ 26 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:58:03

ሦስት ወጣት ኢትዮጵያውያን የኪነ ሕንጻ ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄደ ውድድር ከአሸናፊዎቹ መካከል ለመሆን ችለዋል። ወጣቶቹ በዓለም ታዋቂ የሚባሉ አርክቴክቶች በዳኝነት በተሰየሙበት በፍልስጤም ዌስት ባንክ ግዛት፣ 'ካን አል አህማር' መንደር ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ተንቀሳቃሽ ትምህርት ቤት በመንደፍ ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ተሳትፈው ነው ያሸነፉት።

በኢራን ግዙፍ የንግድ ወደብ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ፍንዳታ 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ800 በላይ ቆሰሉ

እሑድ 27 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 11:24:31

ከአየር ላይ የተቀረፁ ምስሎች ቢያንስ ሦስት የተለያዩ ቦታዎች ቃጠሎው መስፋፋቱን የሚያሳዩ ሲሆን የኢራን አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትርም እሳቱ ከኮንቴይነር ወደ ኮንቴይነር እየተስፋፋ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የሁለት ዓመቷ አሜሪካዊት 'ያለምንም ምክንያት' ተጠርዛ ወደ ሆንዱራስ ሳትላክ እንዳልቀረች ተገለጸ

እሑድ 27 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 6:27:30

ዳኛ ቴሪ ዳውቲይ እንዳሉት 'ቪኤምኤል' በሚል መለያ የምትጠራው ሕጻን ያለምንም ትርጉም ያለው የሕግ ሂደት ተጠርዛ ተልካ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬ አለ።

ከታይታኒክ መርከብ አደጋ የተረፉ ግለሰብ የጻፉት ደብዳቤ በ400 ሺህ ዶላር ተሸጠ

እሑድ 27 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 7:38:38

የደብዳቤው አጫራች እንዳሉት ደብዳቤው ከሌሎች በታይታኒክ ላይ ከተጻፉ ማስታወሻዎች ከፍተኛ ዋጋ መሳብ ችሏል።

ኢትዮጵያዊው ካርዲናል የሚሳተፉበት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ምርጫ እንዴት ይካሄዳል?

ረቡዕ 23 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:56:32

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ የነበሩት የፖፕ ፍራንሲስ ቀብር በመጪው ቅዳሜ ከተከናወነ በኋላ በዓለም ዙሪያ ያሉ የቤተክርስቲያኗ ካርዲናሎች አዲስ ጳጳስ ለመምረጥ በቫቲካን ይሰበሰባሉ። ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያዊው ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል አንዱ ናቸው። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለስምንት መቶ ዓመታት የቆየው አዲስ ጳጳስ የመምረጥ ሂደት እንዴት ይከናወናል?

ግብፅ እና ጂቡቲ የቀይ ባሕር አስተዳደር የተጎራባች ሀገራት "ብቸኛ ኃላፊነት" እንደሆነ መስማማታቸው ተገለጸ

ሐሙስ 24 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 7:44:23

ግብፅ እና ጂቡቲ፤የቀይ ባሕር እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ "የአስተዳደር እና የፀጥታ" ጉዳይ የውሃ አካላቱን የሚጎራበቱ ሀገራት "ብቸኛ ኃላፊነት" እንደሆነ መስማማታቸውን የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል ሲሲ ተናገሩ። ትናንት ረቡዕ ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም. ለይፋዊ የአንድ ቀን ጉብኝት ወደ ጂቡቲ ተጉዘው የነበሩት የግብፅ ፕሬዝዳንት አልሲሲ፤ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡማር ጊሌ ጋር ተገናኝተው ንግግር አድርገዋል።

ከጦርነት የሚሸሹ ሱዳናውያን በሕይወት ለመቆየት ከሰል እና ቅጠል እየበሉ መሆኑ ተነገረ

ቅዳሜ 26 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:58:53

የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሱዳናውያን ተፈናቃዮች ነፍሳቸውን ለማቆየት የዛፍ ቅጠል እና ከሰል እየበሉ መሆናቸውን አንድ የእርዳታ ድርጅት ለቢቢሲ ተናገረ። በኤል ፋሸር ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ተርፈው የሸሹ ሰዎች ምግብ ለማግኘት ባለመቻላቸው ነው ያገኙትን ለመብላት የተገደዱት ተብሏል።

በምሥራቅ ጎጃም በተፈጸመ የድሮን ጥቃት "ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን" የዓይን እማኞች ተናገሩ

ረቡዕ 23 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 8:22:53

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናውጋ ወረዳ ገደብ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሐሙስ ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም. በትምህርት ቤት ዙሪያ በደረሰ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። የአካባቢው አስተዳደር ግን ጥቃቱ በአካባቢው ተሰብስበው በነበሩ የፋኖ ታጣቂዎች ላይ እንጂ በንፁሃን ላይ አለመፈጸሙን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

በቢሾፍቱ ስለሚገነባው ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ አንዳንድ እውነታዎች

ሐሙስ 24 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:00:48

የሚያስተናግዳቸው መንገደኞች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ የመጣው የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አሉ ከሚባሉ አየር ማረፊያዎች የዋነኛው ይሆናል የተባለውን ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ያስጀምራል። በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ ግንባታው የሚካሄደው አየር ማረፊያው በመጀመሪያ ዙር ግንባታው በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል።

አስር ሴቶች፣ አንድ ወንድ፡ በኢትዮጵያ አነጋጋሪ የሆነው የመተጫጨት የቴሌቪዥን ሾው 'ላጤ'

ሰኞ 21 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 6:19:56

አንድ ወንድ እና ሴት ይገናኛሉ። ሴቲቱ በወንዱ ፍቅር ትወድቃለች። በወንዱ ዙሪያ የሚያንዣብቡ እና በፍቅር ለመማረክ የሚሞክሩ ተቀናቃኞችን ትከላከላለች። በስተመጨረሻም ወንዱ ለፍቅሯ እጁን ይሰጣል። ይህ በዩቲዩብ ሲቀርብ የነበረው ትርዒት ባለፉት ወራት በኢትዮጵያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። በርካቶች ከባህል ተቃራኒ ነው ብለው ሲተቹ፣ ሌሎች ደግሞ በአውንታዊ መልኩ ድጋፋቸውን ሲገልጹ ነበር።

የኤርትራው ተቃዋሚ ብርጌድ ንሓመዱ፤ የአዲስ አበባ ቢሮውን ለወታደራዊ "ማዕከላዊ ጽህፈት ቤትነት" የመጠቀም ዕቅድ እንዳለው አስታወቀ

ሐሙስ 17 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:00:04

የኤርትራው የተቃውሞ እንቅስቃሴ "ብርጌድ ንሓመዱ" በአዲስ አበባ ከተማ የከፈተው ቢሮ፤ "በቀጣይ ወታደራዊ ማዕከሎች ሲቋቋሙ፤ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት" ሆኖ እንደሚያገለግል ገለጸ። የተቃውሞ እንቅስቃሴው በኢትዮጵያ "ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ማዕከሎች" ሊኖሩት እንደሚችልም አስታውቋል።

ከሁለት ዓመት የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ዳግም ለሁለት የመከፈል አደጋ የተጋረጠባት ሱዳን

ሐሙስ 17 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:01:30

ከሁለት ዓመት የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ዳግም ለሁለት የመከፈል አደጋ የተጋረጠባት ሱዳን

በቀን ምን ያህል ጊዜ መጸዳጃ ቤት ይሄዳሉ? ዓይነ ምድራችን ስለጤናችን ምን ያመለክታል?

ሰኞ 21 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:55:13

እርስዎ በቀን ስንት ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ይሄዳሉ? አንዴ? ሁለቴ? ወይስ አልፎ አልፎ? ለመሆኑ ዓይነ ምድር ስለ ጤናዎ ምን ያናገራል?

"በእርግጠኝነት በትግራይ ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ እቀጥላለሁ" - ጌታቸው ረዳ

ሐሙስ 10 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 10:51:54

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸውን ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ያስረከቡት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቃለ መጠይቁ ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ ሲመሩት የነበረው ጊዜያዊ አስተዳደር ስላጋጠሙት ተግዳሮቶች ተናግረዋል። ስለ አዲሱ ፕሬዝዳንት ሌተናንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ያላቸውን ግምገማም አጋርተዋል። አዲሱ ፕሬዝዳንቱ ለየትኛዎቹ ጉዳዮች ቅድሚያ ሊሰጡ እንደሚገባ እና ሊያጋጥማቸው ስለሚችሉ ተግዳሮቶችም ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው ወደፊት ሊኖራቸው ስለሚችለው ፖለቲካዊ ተሳትፎም ተናግረዋል።

ስለ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ብዙዎች የማያውቋቸው አምስት እውነታዎች

ማክሰኞ 22 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 8:33:35

ከአንድ ቢሊዮን በላይ ተከታይ ያላት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት የፍራንሲስ ሞት ከእምነቱ ተከታዮች ባሻገር ከፍተኛ ሐዘን ፈጥሯል። ቀለል ባለ የሕይወት ዘይቤ የሚታወቁት ፖፕ ፍራንሲስ ወደ ጵጵስና ማዕረግ ከመድረሳቸው በፊት ውጣ ውረዶችን አልፈዋል። በጳጳሱ የ88 ዓመታት ሕይወት ውስጥ ብዙዎች የማያውቋቸውን አምስት ነገሮች እነሆ . . .

ዕድገት በኅብረት ዘመቻ፡ የሦስቱ ጓደኛሞች የ50 ዓመታት ትዝታ

ቅዳሜ 19 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:57:24

ወታደራዊው አስተዳደር ደርግ የአገሪቱን የመሪነት መንበር ከያዘ በኋላ የዛሬ 50 ዓመት የዕድገት በኅብረት ዘመቻን አወጀ። በዚህም ከ10ኛ ክፍል እስከ ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎች እና መምህራን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተሰማርተው በማስተማር እና በልማት ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ አድርጎ ነበር። በዚህ ዘመቻ የተሳተፉ የዚያ ዘመን አፍላ ወጣቶች ከአምስት አሥርታት በኋላ በጋራ ተሰባስበው ያሳለፉትን ጊዜ አስታውሰዋል። ትዝታቸውንም ለቢቢሲ አጋርተዋል. . .

ለኢትዮጵያውን ዶሮ አርደው 12 ብልቶችን በማውጣት የተካኑት ኬንያውያን

እሑድ 20 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 5:03:07

በጎረቤት አገር ኬንያ ናይሮቢ ውስጥ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ከመኖራቸው የተነሳ የዶሮ ነጋዴዎች ፍላጎታቸውን በመረዳት 'የሐበሻ' ዶሮዎችን እና እንቁላልን ያቀርባሉ። በተጨማሪም ኬንያውያኑ ዶሮዎቹን አርደው ኢትዮጵያውያኑ በሚፈልጉት ዓይነት 12 ብልት በማውጣት አገልግሎት ይሰጣሉ። እኛም ትንሳዔ በዓልን ምክንያት አድርገውን ለኢትዮጵያውያኑ ዶሮ አርደው በሚፈልጉት መልኩ ከሚያርቡት መካከል አንዱን ተመልክተናል።

ሚሊዮኖች የደም ግፊት እንዳለባቸው አያውቁም፤ ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለብዎ ለማወቅ የሚረዳ ቀላል ዘዴ

ረቡዕ 16 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:34:46

በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባቸው 1.3 ቢሊዮን ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ የጤና ችግሩ እንዳለባቸው አያውቁም። በዓለም ጤና ድርጅት ደረጃ መሠረት የአንድን ሰው ለከፍተኛ የደም ግፊት ያለውን ተጋላጭነት ለማወቅ፣ የደም ግፊት ልኬት ንባብ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት እና ጤናን ለመጠበቅ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ለማወቅ ይህንን ዘዴ ይሞክሩ። ለቤትሰብዎ፣ ለጓደኞችዎ፣ ለሚያውቋቸው እና ጤና ለሚመኙላቸው በሙሉ ያጋሩ።

የአእምሮ ዕድገት መዛባት (ኦቲዝም) ያለባቸው መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚረዳ ጥናት ለኳታር ያቀረቡት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ

ረቡዕ 2 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:04:10

ዛሬ፣መጋቢት 24 የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው። ይህ ዕለት በዓለም ደረጃ ታስቦ እንዲውል ለተባበሩት መንግሥታት ሐሳብ ያቀረበችው ኳታር ናት። ወደዚያው ብናቀና ዶክተር ወንድወሰን ግርማን እናገኛለን። ኦቲስቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚያስችል ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ናቸው።

ከምሽት ክበብ 'ጋርድነት' እስከ ጵጵስና - የሮማው ሊቃነ-ጳጳስ ፍራንሲስ አስገራሚ የሕይወት መስመር

ሰኞ 21 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 8:32:14

በጠና ታምመው ሰንብተው ሰኞ ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም. ሕይወታቸው ያለፈው ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ታሪካቸው ደማቅ እና ጉራማይሌ ነው። ይህንን ቦታ ለመያዝ ከደቡባዊ ንፍቀ ክበብ መሆናቸው እንዲሁም ከአሜሪካ ክፍለ አህጉር መምጣታቸው የመጀመሪያ ያደርጋቸዋል። የእግር ኳስ ወዳጅ፣ የምሽት ክበብ ጥበቃ እና የጽዳት ሠራተኛ የነበሩት ጳጳሱ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው በዓለም የተከበሩ አባት ነበሩ።

ከአህያ ወተት የሚገኘው እና አንድ ኪሎ 170 ሺህ ብር የሚሸጠው  አይብ

ሐሙስ 10 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:59:09

ሰርቢያ ውስጥ ከአህያ ወተት የሚገኝ አንድ ኪሎ ግራም አይብ 1200 ዩሮ ይሸጣል። ይህ ዋጋ ከአማካይ ሰርቢያዊያን ወርሀዊ ደመወዝ ላቅ ያለ ነው

ቤቶቻቸውን ሲያጸዱ በማህበራዊ ሚዲያዎች በማሳየት ገንዘብ ማፍራት የቻሉት ግለሰቦች

ማክሰኞ 8 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:48:24

እንደ በርካታ ወላጆች የዩናይትድ ኪንግደም ነዋሪዋ ካሪስ ሃርዲንግ ረጅም ጊዜዋን የምታሳልፈው ልጆቿን በመንከባከብ ነው። ነገር ግን የ27 ዓመቷ የሶስት ልጆች እናት ከሌሎች ለየት የሚያደርጋት ቤቷን ስታጸዳ፣ ስትወለውል፣ ስትጠርግ፣ አንዱን ስታነሳ ስትጥል፣ ስታዘጋጅ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ይመለከቷታል።

ከእህቷ በተለገሰችው ማህጻን አማካኝነት ወልዳ ለመሳም የበቃችው ሴት

ዓርብ 11 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:57:08

ከእህቷ በተለገሰችው ማህጻን ጽንስ በመያዝ ለመውለድ የበቃችው ሴት በዚህ መንገድ ልጅ በመታቀፍ በዩናይትድ የመጀመሪያዋ እናት ሆናለች። የጨቅላዋ እናት ጽንስ ለመቋጠር የሚያስችላት ማህጸን በተፈጥሮ ስላልነበራት ከእህቷ የተለገሳት ማህጻን በአገሪቱ የመጀመሪያው በሆነ ስኬታማ ንቅለ ተከላ አግኝታ ነው ለመውለድ የበቃችው።

በመድኃኒት እስከ 38 ኪሎ ውፍረት የቀነሱ ሴቶች ስለ ልምዳቸው ምን ይላሉ?

ሰኞ 7 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:03:06

ከመጠን በላይ ውፍረት ከስንፍና እና ከአስቀያሚነት ጋር በሚያይዝባት ዓለም በርካቶች በውፍረታቸው ምክንያት ይሸማቀቃሉ፣ መድልዎም ይደርስባቸዋል። ከመጠን በላይ ወፍራም የነበረችው ብራኔይሻ ኩፐር ለየት ያለ ፍጡር ነኝ የሚል ስሜት ይሰማት ነበር።

የምንጠቀማቸው 'የሜክአፕ' ዕቃዎች ምን ያህል አደገኛ እና የተበከሉ ናቸው?

ቅዳሜ 5 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:37:30

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የምንጠቀመው 'ሜክአፕ' የመገልገያ ጊዜው መች እንደሚያበቃ አጣርተን እናውቃለን? ጊዜያቸው ያለፈባቸው ሜክአፖች ምን ያክል አደገኛ እንደሆኑስ የምናውቀው ነገር አለ? ሜክአፕ የሚጠቀሙባቸውን ብሩሾች ያፀዳሉ?

አብዛኞቹ ነዋሪዎቿ ዩቲዩበር የሆኑባት መንደር

ረቡዕ 26 ማርች 2025 ጥዋት 3:38:18

በመንደሩ ወደ 4,000 ሰዎች ይኖራሉ። 1,000 ያህሉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከዩቲዩብ ጋር የተያያዘ ሥራ አላቸው። በመንደሩ ውስጥ ቪድዮ ያልተቀረጸ ሰው ማግኘት ከባድ ነው። ከዩቲዮብ በሚገኘው ገቢ የመንደሯ ምጣኔ ሃብት አድጓል። በመንደሩ እኩልነት እንዲሰፍንና ማኅበራዊ ለውጥ እንዲመጣም አግዟል።

"ሆስፒታል ውስጥ ከሌላ ልጅ ጋር መቀያየሬን በ70 ዓመቴ አወቅኩ"

እሑድ 6 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:56:49

ሱዛን የዘረ መል መመርመሪያ መሣሪያ ገዝታ ነበር በቤቷ ምርመራ ያደረገችው። ውጤቱን ስታይ ማመን ተሳናት። አሁን በ70ዎቹ አጋማሽ ላይ ትገኛለች። ስለ አያቷ ብዙም አታውቅም ነበር።

በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰት እብጠት ሁሉ ኪንታሮት ነው? ኪንታሮት ካልታከመ ምን ያስከትላል?

ሰኞ 28 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:53:45

የፊንጢጣ ኪንታሮት ሰዎች ብዙም የማይነጋገሩበት ህመም ነው። አንዳንዶች ሐኪም ለማማከርም ሲያመነቱ ይስተዋላል። ለመሆኑ በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰት እብጠት እና ህመም ሁሉ ኪንታሮት ነው? ሕክምና የሚያስፈልገውስ መቼ ነው? ካልታከመስ ምን ያስከትላል?

በቀን ምን ያህል ጊዜ መጸዳጃ ቤት ይሄዳሉ? ዓይነ ምድራችን ስለጤናችን ምን ያመለክታል?

ሰኞ 21 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:55:13

እርስዎ በቀን ስንት ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ይሄዳሉ? አንዴ? ሁለቴ? ወይስ አልፎ አልፎ? ለመሆኑ ዓይነ ምድር ስለ ጤናዎ ምን ያናገራል?

ስለምንመገበው ጥሬ ሥጋ ማወቅ ያሉብን ነገሮች እና ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ

እሑድ 20 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 5:01:58

በዓላትን ከሚያደምቁ ነገሮች መካከል ምግብ እና መጠጦች ከፍ ያለ ድርሻ አላቸው። በተለይ እንደ ፋሲካ ያሉ ዓውደ ዓመቶች የሚመጡት ረዥም የጾም ወቅትን ተከትለው በመሆናቸው አቅም በፈቀደ ሁሉ እርድ ይከናወናል። በተለይ ደግሞ ጥሬ ሥጋ የበርካቶች ምርጫ ነው። ጥሬ ሥጋን በተመለከተ ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን?

ሚሊዮኖች የደም ግፊት እንዳለባቸው አያውቁም፤ ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለብዎ ለማወቅ የሚረዳ ቀላል ዘዴ

ረቡዕ 16 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:34:46

በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባቸው 1.3 ቢሊዮን ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ የጤና ችግሩ እንዳለባቸው አያውቁም። በዓለም ጤና ድርጅት ደረጃ መሠረት የአንድን ሰው ለከፍተኛ የደም ግፊት ያለውን ተጋላጭነት ለማወቅ፣ የደም ግፊት ልኬት ንባብ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት እና ጤናን ለመጠበቅ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ለማወቅ ይህንን ዘዴ ይሞክሩ። ለቤትሰብዎ፣ ለጓደኞችዎ፣ ለሚያውቋቸው እና ጤና ለሚመኙላቸው በሙሉ ያጋሩ።

የምንጠቀማቸው 'የሜክአፕ' ዕቃዎች ምን ያህል አደገኛ እና የተበከሉ ናቸው?

ቅዳሜ 5 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 4:37:30

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የምንጠቀመው 'ሜክአፕ' የመገልገያ ጊዜው መች እንደሚያበቃ አጣርተን እናውቃለን? ጊዜያቸው ያለፈባቸው ሜክአፖች ምን ያክል አደገኛ እንደሆኑስ የምናውቀው ነገር አለ? ሜክአፕ የሚጠቀሙባቸውን ብሩሾች ያፀዳሉ?

የኢየሱስ ስቅለት እና ሞት በሕክምና ባለሙያዎች ዓይን እንዴት ይተነተናል?

ዓርብ 18 ኤፕሪል 2025 ጥዋት 3:59:05

በአይሁዶች እና ሮማውያን ችሎት ወንጀለኛ ተብሎ የቆመው ኢየሱስ ክርስቶስ በጥፊ ተመትቷል፣ ተገርፏል፣ ተራቁቷል፣ የእሾህ አክሊል ተደፍቶበታል። ኢየሱስ ከተያዘበት እስከ አርብ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ስቃይ ደርሶበታል። በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ብዙ ደም ፈስሶታል። ተጠምቷል። ከዚያም ሞቷል። የሕክምና ባለሙያዎች ኢየሱስ የደረሰበትን እንግልት፣ ድብደባ እና ስቅላት ከሙያቸው አንጻር እንዲህ ተንትነውታል።

'ዝምተኛው ገዳይ' በኢትዮጵያ

ዓርብ 28 ማርች 2025 ጥዋት 4:04:02

የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ የአየር ብክለት ልኬት ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል። ድርጅቱ እንደሚለው 99 በመቶው የዓለም ሕዝብ የሚተነፍሰው አየር ተበክሏል። ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚዳርገው የአየር ብክለት በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሙያ ይናገራሉ። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ዋነኛ አየር በካዮች የትኞቹ ናቸው? መፍትሔውስ ምንድን ነው?

በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ክፉኛ አቁስላ፣ ማርካ ያከመችው የጁባላንዱ ፕሬዚዳንት ማዶቤ

ሰኞ 17 ማርች 2025 ጥዋት 3:41:37

"የብዙ ኢትዮጵያዊ ደም ነው የወሰደው። የኢትዮጵያ ደም ነው ያለህ እንለዋለን" ይህ በሶማሊያ የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ለአሁኑ የጁባላንድ ግዛት ፕሬዚዳንት ማዶቤ በቀልድ መልኩ ጣል ያደርጉላቸው ነገር ነው። ይህ በቀልድ የተለወሰ መሪር እውነታ ነው። እውነታው የሶማሊያዋን ራስ ገዝ ጁባላንድን ላለፉት 12 ዓመታት ያስተዳደረው ማዶቤ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ጦር ክፉኛ ቆስሎ በአዲስ አበባ ህክምና አድርጓል።

“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት

ሰኞ 18 ኖቬምበር 2024 ጥዋት 3:53:07

ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።

ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ

ሰኞ 30 ሴፕቴምበር 2024 ጥዋት 4:13:42

ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ (ዶክትሬት) የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ እና ታሪክን በሚወክሉ በአምስት መምህራን ተወክሎ ቀርቧል።

"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ

ዓርብ 7 ማርች 2025 ጥዋት 3:50:04

ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?

"ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድም፤ አገራችን ሕዝባችን ነው፤ ዝም አንላቸውም" - ጃዋር መሐመድ

ሐሙስ 19 ዲሴምበር 2024 ጥዋት 4:54:19

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም ነው።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል። ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።

በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ

ዓርብ 24 ሜይ 2024 ጥዋት 4:16:17

ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።

ለአራት ዓመታት ከኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች ጋር በመኖር የተቀረጸው ፊልም፡ ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’

ሰኞ 16 ዲሴምበር 2024 ጥዋት 4:18:56

የዘጋቢ ፊልሙ ደራሲ እና አዘጋጆች ማክስ ደንካን እና ዘንየን ዩ ናቸው። ከፕሮዲውሰሮቹ አንዷ ታማራ ማርያም ዳዊት ናት። ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’ በዋርሶው ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል፣ በትሪቤካ ፊልም ፌስቲቫል፣ በሼፊልድ ኢንተርናሽናል ዶክመንተሪ ፌስቲቫል እና በሌሎችም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ዕውቅና አግኝቷል። ፊልሙ የቻይና ባለ ሃብቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ሥራ አጥነትን፣ ባህልን፣ ቤተሰብን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የአርሶ አደሮች የተጠቃሚነት ጥያቄን በዋናነት ይዳስሳል።

የኩላሊታችንን ጤና ለመጠበቅ የሚያግዙ 6 ቀላል መንገዶች

ዓርብ 29 ማርች 2024 ጥዋት 4:06:46

በኢትዮጵያ በስፋት እየተስተዋሉ ከሚታዩ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች መካከል የኩላሊት ችግር አንዱ እየሆነ መጥቷል። ወሳኝ ከሆኑት የሰውነት ክፍሎች መካከል አንዱ የሆነው ኩላሊት በተለያዩ ምክንያቶች እክሎች ይገጥሙታል። ነገር ግን የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር እና ጥንቃቄ በማድረግ ጤናማ ኩላሊት እንዲኖረን ማድረግ ይቻላል። ከእነዚህም መካከል ለኩላሊት ጤና የሚረዱ ስድስት ቀላል ጥንቃቄዎችን እነሆነ. . .

የላጤዎች ጉባኤ በቦሌ

ቅዳሜ 16 ኖቬምበር 2024 ጥዋት 4:43:38

በፈረንጅ አፍ ‘ስፒድ ዴቲንግ’ ይባላል። የአማርኛ አቻ የለውም። በአቋራጭ መተጫጨት ነው-ነገሩ። ፖለቲካዊ ቋንቋ ይመስልብናል እንጂ ‘የትዳር ማሳለጫ’ ሊባል ይችላል። ነገሩ ‘የፍቅር-ጉድኝት’ ለመፍጠር የሚደረግ አጭር ጉዞ ነው። የፍቅር ጓደኛ ለማግኘት አደን እንደመውጣት ያለ ነው። የትዳር አሰሳ. . . የወደፊት ውሃ አጣጭን ለማማለል የሚሰጥ የአምስት ደቂቃ ፍጹም ቅጣት ምት ነው። የት? አዲስ አበባ ቦሌ ላይ. . .

ምሥሎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዴት ይሠራሉ? ከእውነተኞቹስ እንዴት መለየት ይቻላል?

ማክሰኞ 19 ዲሴምበር 2023 ጥዋት 4:19:42

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) አማካይነት የሚዘጋጁት ምሥሎች ለእውነታ በእጅጉ የቀረቡ በመሆናቸው ምክንያት ትክክለኛ ፎቶዎች ወይም የሰው ልጅ የአእምሮ እና የእጅ ሥራ ውጤት ከሆኑት አንጻር ለመለየት አዳጋች እየሆኑ መጥተዋል። ታዲያ በዚህ ቴክኖሎጂ የተዘጋጁትን ምሥሎች ከእውነተኞቹ እንዴት መለየት እንችላለን?

የተጠጋገኑ እና ኦሪጂናል ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮች እኛንም ስልካችንንም እንደሚጎዱ ያውቃሉ?

ሐሙስ 29 ፌብሩዋሪ 2024 ጥዋት 4:14:38

ሊበጠስ ጫፍ የደረሰ እና የተጠጋገነ የሞባይል ቻርጅ ማድረጊያን መጠቀም ብዙዎቻችን ምንም ጉዳት የሌለው ይመስለናል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ያልተጠበቀ ሲከፋም አሰቃቂ አደጋን ሊያስከትል ይችላል። በጥሩ ሁኔታ ላይ ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮችን መጠቀም ምን ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ? ምን ዓይነት ቻርጀሮችን ብንጠቀም ይመከራል?

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ብቅ ጥልቅ የሚሉት ግዙፎቹ “ባዕድ አብረቅራቂ ወጥ ብረቶች”

ሐሙስ 20 ጁን 2024 ጥዋት 4:08:35

ከቀናት በፊት በአሜሪካ የታየው ግዙፍ ባዕድ ነገር መነጋገሪያ ሆኗል። ነገር ግን ይህ ከስተት የመጀመሪያ ሳይሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ የዓለም ክፍሎቸ ውስጥ ታይተዋል። አመጣጣቸውም ሆነ ምንነታቸውም ለበርካታ መላ ምቶች ክፍት ሆኗል። የሌላ ዓለም ፍጡራን የተከሏቸው፣ የጥበብ ሥራዎች. . . ሌላም ሌላም እየተባሉ ነው። እስካሁን ምን የሚታወቅ ነገር አለ?